Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መድህኔ

Medhene

2017 · ትራክ 7 · 7:07 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኢየሱስ መድህኔ

የተጎሳቆለልኝ ለኔ

ነፍሴን ሊያድናት

እርሱ ሆነ መስዋእት (፪x)

ደሙ ያድናል ደሙ (፫)

የመስቀል ላይ ጣሩ ስቃዩ ህመሙ

ልከፍልው በማልችልው እዳ

በሞት ጥሪ ነፍሴ ተገዳ

ሳዘግም ወደ ሲኦል መንገድ

ከሰማይ ራርቶልኝ እግዚአብሔ

ውድና አንድ ልጁን ላከልኝ

በኔ ፈንታ እንዲታረድልኝ

ሳያቅማማ መጣ ኢየሱሴ

አመለጠች ከሲኦል ነፍሴ

አለብኝ ውለታዉ (፪)የሱስ የከፈለዉ

ብር ወርቅ አይደለም ነፍሱን ነዉ(፪x)

ተጠምቶ ሲጠጣ መራራ

ሲከፍል የኔን ስቃይ መከራ

የሾህ አክሊል ጭኖ በራሱ

ሲጨነቅ እስክታልፍ ነፍሱ

ቀና ብሎ ሲያይ ወደ አባቱ

ጨክኖ አዞረበት ፊቱን

አንገቱን ደፍቶ ስለእኔ

ተፈጸመ አለ መድህኔ

ኢየሱስ መድህኔ

የተጎሳቆለልኝ ለኔ

ነፍሴን ሊያድናት

እርሱ ሆነ መስዋእት (፪x)

ደሙ ያድናል ደሙ (፫)

የመስቀል ላይ ጣሩ ስቃዩ ህመሙ

ስለምን ይሆን ይሄ ጌታ

ያጣጣረው በዚያ ጎልጎታ

የተሰደበ የተተፋበት

ባልሰራው ባልፈጸመው ሃጢያት

ለካ ስለ እኔ ነው ቤዛ

ነፍሱን ከፍሎ ነፍሴን የገዛ

ቃል የማይገልጸው ድንቅ ፍቅሩ

ገለጠልኝ በመስቀል ጣሩ

አለብኝ ውለታዉ (፪)የሱስ የከፈለዉ

ብር ወርቅ አይደለም ነፍሱን ነዉ(፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ