Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ ትልቅ

Ante Tilik

2017 · ትራክ 6 · 4:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የሚያስፈራው ግርማህ ሲያበራ

ተንቀጠቀጠ ጨሰ ተራራ

የታላቅነትህ ክብር ሲያርፍበት

ሊቋቋም አልቻለም የአንተን ዉበት

አንተ ትልቅ ነህ

አንተ ኃይለኛ

የሰልፉ አሸናፊ ሁሌም ፊተኛ

አንተ ብርቱ ነህ

አንተ ገናና

በሰማይ በምድር ሁሉ ባለዝና

ስምህን እባርካለው (፬X)

የአንተን ታላቅነት ሞገስን እያየው

ስምህን እባርካለው

አደራረግሀን ጥበብን እያየው

ስምህን እባርካለው

ስምህን እባርካለው (፬X)

የአንተን ታላቅነት ሞገስን እያየው

ስምህን እባርካለው

አደራረግሀን ጥበብን እያየው

ስምህን እባርካለው

አንተ ትልቅ ነህ

አንተ ኃይለኛ

የሰልፉ አሸናፊ ሁሌም ፊተኛ

አንተ ብርቱ ነህ

አንተ ገናና

በሰማይ በምድር ሁሉ ባለዝና

የቃልህን ሥልጣን ያሳይ ፍጥረቱ

ውኃ ፈለቀ ወጣ ከአለቱ

መልስን ይሰጥሃል ባሕር አድምጦ

ሕዝብህን ሊያሻግር ጠላትን ውጦ

አንተ ትልቅ ነህ

አንተ ኃይለኛ

የሰልፉ አሸናፊ ሁሌም ፊተኛ

አንተ ብርቱ ነህ

አንተ ገናና

በሰማይ በምድር ሁሉ ባለዝና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ