በስግደት
Besigdet
2017 · ትራክ 11 · 5:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በስግደት በአምልኮ በብዙ ምሥጋና
በዕውነት በመንፈስ ፊትህ ልምጣና
ላምልክህ እንደገና (፫)
እንደወራጅ ዉሃ ልክ እንደጅረቱ
አይቋረጥብህ አምልኮዬ ፊቱ
ይፍሰስ በማለዳው ይፍሰስ በሌሊቱ
መሳይ ስለሌለው ጌታ ጌትነቱ (፪)
አዝማች · Chorus
ላምልከው በአምልኮዬ
ላክብረው በዝማሬዬ
ላግንነው በዕልልታዬ
ላድምቀው በጭብጨባዬ
ይገባዋል እና ጌታዬ (፬)
ቁጥር 2 · Verse 2
የመውደዴን ልኩን የፍቅሬን መግልጫ
ካለኝ ነገር ሁሉ የምሰጠው ብልጫ
ለሕይወቴ ጌታ ለነፍሴ ንጉሥ
አለኝ የምሰዋው ከነፍሴ የሚፈስ
የቅኔው የዜማ ሽታ ታጅቦ በብዙ ሆታ
ከምድር ይውጣ ያስተጋባ ወደ አንተ ማደሪያ ይግባ
ይገባሃል እና ጌታዬ (፬)
አዝማች · Chorus
በስግደት በአምልኮ በብዙ ምሥጋና
በዕውነት በመንፈስ ፊትህ ልምጣና
ላምልክህ እንደገና (፫)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ