ተነሳ
Tenesa
2017 · ትራክ 8 · 4:12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አላመልክም ሞቶ የቀረ የተነሳውን ነው እንጂ
እውነት ነው ሞቶ ነበር ግን ተነስቷል የእኔ ወዳጅ
ገደልነው ብለው ቢያወሩ አኑረነዋል ከመቃብር
በሶስተኛው ቀን ተነሳ በትንሳኤው ታላቅ ክብር
ተነሳ ሞት ተሸነፈ ተነሳ ኃይል አጣ ከቶ
ተነሳ በኢየሱስ ላይ ተነሳ መቼ በርትቶ
ተነሳ ከፍ ከፍ አለ ተነሳ ወጣ ወደላይ
ተነሳ በአባቱ ቀኝ ተነሳ ከብሯል በሰማይ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱሴ ኢየሱስ ኢየሱሴ
ቁጥር 2 · Verse 2
በትንሳኤው ቀን ማለዳ ባዶ ነበር መቃብሩ
ሕያው ሆኖ እንደወጣ መላእክቱ መሰከሩ
ሃዋርያቱም አስታወሱ የተሰጣቸውን ተስፋ
ጊታቸው ሞቶ እንደማይቀር እንደ ሌሎች እንደማይጠፋ
ተነስቷል ሞት ተሸነፈ ተነስቷል ኃይል አጣ ከቶ
ተነስቷል በኢየሱስ ላይ ተነስቷል መቼ በርትቶ
ተነስቷል ከፍ ከፍ አለ ተነስቷል ወጣ ወደላይ
ተነስቷል በአባቱ ቀኝ ተነስቷል ከብሯል በሰማይ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱሴ ኢየሱስ ኢየሱሴ
ቁጥር 3 · Verse 3
የትንሳኤው ምስክሮች አይተውታል በዓይናቸው
በመካከላቸው ቆሞ ሰላም ለእናንተ ሲላቸው
በእጆቻቸው ዳስሰዋል የችንካሩን ምልክት
በእርግጥም ያ ኢየሱስ የተነሳው ነው ከሞት
ተነሳ እንደ ሌኡቹ ተነሳ አልቀረም በምድር
ተነሳ የእኛ ኢየሱስ ተነሳ ወጥቷል በክብር
ተነሳ ይመርመር ይታይ ተነሳ ታሪክ ይጠና
ተነሳ እንደ ጌታችን ተነሳ ሌላ የለምና
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱሴ ኢየሱስ ኢየሱሴ
ቁጥር 4 · Verse 4
ቢጠብቁ ቢያስጠብቁ መቃብሩ ላይ አትመው ኦ
እነሳለሁ ብሎ እንዳለ እንዳይነሳ እናድርግ ብለው ኦ
እንኳን ሥጋ ለባሽ ቀርቶ አልቻለችውም ምድሪቱ ኦ
ሕያው ሆኖ አሸንፏል በቃ ይኸው ነው እውነቱ ኦ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ