ምሥጋናው ይታወጅ
Misganaw Yitawej
2017 · ትራክ 10 · 4:23 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
በአደባባዩ በቤቱ ደጅ
ምሥጋናው ይታወጅ
በክብር ቤቱ ዙፋኑ ዙሪያ
ይዘመር ሃሌሉያ
ቁጥር 1 · Verse 1
በልቤ ሞልቶ የተረፈው
የምሥጋን ቃል ዝማሬ ነው
መክፈል ባልችልም የእርሱን ውለታ
ፊቱ ቀርቤ ላሰማ ዕልልታ
ላደረገልኝ ለሰራው ሁሉ
ወዳጅ ዘመዴ ክበር ይበሉ
በጸሎት ምልጃ ለቃተታችሁ
ዛሬ ምሥጋና ቀን ነው አይዟችሁ
አዝማች · Chorus
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
በአደባባዩ በቤቱ ደጅ
ምሥጋናው ይታወጅ
በክብር ቤቱ ዙፋኑ ዙሪያ
ይዘመር ሃሌሉያ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለቴን ልክፈል ቃል ኪዳኔን
ለክብርህ ቢሆን ብዬ ያልኩትን
ባይመጣጠን ከአንተ ውለታ
ግን ዝም አልልም ልሰዋው ላምጣ
ጣልቃ እየገባ በሕይወት መንገዴ
የመራኝ እጅህ ክንድህ አይደል እንዴ
ታዲያ ስለምን ዕልልታን ልርሳ
ይልቅ ልጨምር ላብዛ ሙገሳ
አዝማች · Chorus
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
ወደ አምላኬ ቤት ወደ ማደሪያው
አለኝ ምሥጋና ይዤ የምገባው
ወደ አምላኬ ቤት ወደ መቅደሱ
አለኝ አምልኮ የሚሆን ለእርሱ
በአደባባዩ በቤቱ ደጅ
ምሥጋናው ይታወጅ
በክብር ቤቱ ዙፋኑ ዙሪያ
ይዘመር ሃሌሉያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ