Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድል ለማድረግ ወጣ

Del Lemadreg Weta

ትራክ 6 · 2:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የፈርዖን ገንዘብ ያልማረከው ጀግና

ዓይኑ ያልደከመ ያላለቀ ገና

ድል ለማድረግ ወጣ በጦርነት ሲቃ

በጀርባው አንግቦ የአምላኩን ጦር ዕቃ (፪x)

የወይኒው አስራት የግርፋት ብዛት

አልቻለው ሊያበርደው የፍቅሩን ትኩሳት

ፎከረ ያ ጐበዝ ሊጥል ሊገረስስ

ጠምዶ በቀኝ እጁ የቃሉን መትረየስ (፪x)

የልብ ዓይኑ ፈጦ ትኩር ብሎ እያየ

የጠላትን ምሽግ ሰፈሩን አጋዬ

የአርያም እሳት በኃይል ጐብኝቶታል

እባቡና ጊንጡን ከእግሩ ስር ረግጦታል (፪x)

በድካም በረታ ጅማቱ ጠንክሯል

አንገብግቦት ፍቅሩ ወኔው ተቀስቅሷል

በጀርባው መተልተል ጌታን አከበረ

የሞትንም ባሕር በእምነት ተሻገረ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ