Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መጥቷል በንስሃ

Metual Beneseha

ትራክ 4 · 4:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሊጠፋ የነበር በኃጢያቱ ረክሶ

ለጥቂት አምልጦ ከዓለም ተመልሶ

ማንነቱን አውቆ ልብ ገዝቶ ኖሮ

ባለፈው ጥፋቱ በጸጸት ተማሮ

መጥቷል በንስሃም የጌታን ቃል ሰምቶ

ሰይጣንን ዓለምን ሥጋን ተሰናብቶ (፪x)

እንዲያው ሲግደረደር ጥማቱን ደብቆ

የጭንቀቱን ግፊት በሆዱ አምቆ

ሰላምን ለማግኘት ሲባዝን ሰንብቶ

ከሰላም አለቃም መንገድ ተገናኝቶ

አሁን ወጥቶለታል ችግሩን ተንፍሶ

ተጽናንቶም ይኖራል ሕይወቱ ታድሶ (፪x)

ወዶታል ከአንጀቱም ተመክቶበታል

ጌታም በጠላት ፊት በዘይት ቀብቶታል

ከትቢያ አንስቶ ሞገስን ሰጥቶታል

በድል አየመራው ከዚህ አድርሶታል

እንደ ሰባ እንቦሳም በደስታ ይዘላል

እየፈነደቀም ሀሌሉያ ይላል (፪x)

ጠቢባን ግንበኞች ወደ ጐን የጣሉት

አይጠቅመንም ብለው በንቀት የካዱት

የናዝሬቱ ኢየሱስ ግን የማዕዘን አለት

ሆኖለታል ለእርሱ የሕይወት መሰረት

ከዳንኩኝስ ብሏል አዲስ ሰው ከሆንኩኝ

ዘመድ ወዳጆቼ ያሉትን ይበሉኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ