መልክህን ጌታዬ
Melkehen Gietayie
ትራክ 1 · 2:55 · አማርኛ
መልክህን ጌታዬ ጸሃይ አክስሎታል
በሃሩሩ ብዛት ከስተህ ገርጥተሃል
ምቾትም ድሎትም አልነበረህም ጌታ
ለሰበዓዊው ፍጥረት በስቃይ ተመታህ (፪x)
የሞት ፅዋ ቀርባ ፈዋሼ ሲጨነቅ
የአባቱ ድምፅ ርቆት በጭንቀት ሲሳቀቅ
አንጀቱ ተጣብቆ አጥንቱ ሰልስሎ
የእኔን ሕይወት ዋጀ ጌታዬ ተጋድሎ (፪x)
ተራራ እየቧጠጥክ በመዳህ ስትወጣ
ሆንክልኝ መድህኔ ስለ እኔ ከርታታ
ለአንተ የጣር ቀን ነው ለእኔ የፈውስ ዕለት
ራስህን አጋልጠህ ፈፀምከው በትዕግሥት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ