ምሥጋና ይገባሃል
Mesgana Yegebahal
ትራክ 8 · 3:18 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይገባሃል የሰራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምሥጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
ቁጥር 1 · Verse 1
የመጀመሪያውና የመጨረሻው
ክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሚመጣው
የእግዚአብሔር በግ የታረድከው
በደምህ እድፈቴን ያጠብከው
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይገባሃል የሰራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምሥጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
እስራታችንን የበጣጠስከው
ቀንበራችንን ደግሞ የሰበርከው
አርነታችንን በደምህ ያወጅከው
በላይ በአባትህ ቀኝ ያለኸው
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይገባሃል የሰራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምሥጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
ቁጥር 3 · Verse 3
ዋጋችንን ልትሰጠን ልታሳርፈን
በማይነገር ሀሴት ልታስደስተን
በጽዮን ውስጥ እፎይ ልታሰኘን
የምትመጣው እኛን ልታጽናናን
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ይገባሃል የሰራዊት ጌታ
ከቶ ማን ተገኝቷል ማኅተሙን ሊፈታ
ምሥጋና ይገባሃል ክብርም ይገባሃል
መወደስ ይገባሃል መንገሥም ይገባሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ