ኃይልን ቀምሼ
Haylen Qemeshie
ትራክ 12 · 3:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃይልህን ቀምሸ ክንድህን አይቼ
ክብርህ ተንሰራፍቶ በዓይኔ ተመልክቼ
ያን ሁሉ ዘነጋሁ ዓለምን አይቼ
ልሄድም ተመከርኩ ከአንተ ተለይቼ
አንተ ግን ጌታዬ ጠብቀኝ ልጅህን
አዝማች · Chorus
እግሬን ልትመልሰው ልትረዳኝ ፍጠን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅርህ ግድ ይለኛል እንዳልለይህ
ኮብልዬም ብጠፋ ከድሎት ደጅህ
ከችጋሩ ሌላ ፀጋ ምህረትህ
አያስጨክኑኝም ትዝታዎችህ
ከቤትህ ሸሽቼ ወዴት እደርሳለሁ
አዝማች · Chorus
ከመንፈስህ ርቄ ወደማን እሄዳለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምድሪቱ:አንገላታኝ አላማዬን ስቼ
ወደ ግራና ቀኝ ዓይኖቼን አንስቼ
ኃጥዕ ሲለመልም ሲቀናው አይቼ
ፍጻሜውን ሳላይ በሥራው ቀንቼ
ፍሬ የሌለው ከንቱ ለካስ ባዶ ኖሯል
አዝማች · Chorus
ግን የእኔው ደስታ ከዓለም ይልቃል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ነፍሴ ተንገድግዳ ልትወድቅ ነበረ
ግን ድጋፍ አገኘች ጠላቴም አፈረ
የምን መታለል ነው ጉዳቴስ የቱ ነው
ተደላድያለሁ ኢየሱስ በቀኝ ነው
አረጋግጦልኛል ጌታ እንደማይተወኝ
አዝማች · Chorus
ጠላት ተስፋ ቁረጥ አትችልም ልትጥለኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ