ከሸካራው መንገድ
Keshekaraw Menged
ትራክ 3 · 2:35 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና ህጻን ሳለህ ስጠነቀቅልህ
ክንዶችህን ይዤ ዳዴ ሳስተምርህ
መራመድን ችለህ ሩጫውን አጠናቅቀህ
እንዳልገሰገስክ ዛሬ ግን ታከተህ
አዝማች · Chorus
ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው
አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው
ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
በሃሩርር ተቃጥለህ በጥም ተመትተሃል
ፍሬህ ሁሉ ደርቆ ፍሬ ቢስ ሆነሃል
መንፈሳዊነትህ አሁን ከአንተ ርቆ
ለስጋ ተገዛህ ፀጋህ ሁሉ አልቆ
አዝማች · Chorus
ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው
አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው
ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ከግብጽም ጀምሬ እኔ አምላክህ ነህ
በደሜ የዋጀሁህ ተው አታሳዝነኝ
ምህረት እንደምወድ ጸባዬን ተውቃለህ
እልሁን ተውና ታረቀኝ ልጄ ነህ
አዝማች · Chorus
ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው
አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው
ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ምህረት ተነስታለች ልቤ ተናውጣለች
እጄ ተዘርግታ ገና ትኖራለች
የፍቅር ቀንበሬን ናና ልጫንብህ
ጫንቃህንም ስጠኝ ዳግም ልረስብህ
አዝማች · Chorus
ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው
አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው
ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ