መብዛት መዋረዱን
Mebzat Mewaredun
ትራክ 13 · 3:33 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን
ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በቃሌ ስበትን በከንፈሬ ተሳስቼ እንዳልጥል
ያገኘሁት መስሎኝ እየከነፍኩ ስሮጥ ወደ ክፋት
ሰው ሁሉ አስፈርቶኝ ስቅበዘበዝ አግኝቶኝ ያ ጌታ
እብድነቴን ገፎት ቤት ሰጠኝ አገኘሁ ይቅርታ
አዝማች · Chorus
መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን
ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደ ሰባ እንቦሳ ስፈነጥዝ በተራራ ሕይወት
ተመስገን እያልኩኝ ኢየሱስን በበረከት ምንጮች
ከዛም ሳላስበው በመቅሰፍት በሸለቆ ስገኝ
ተሰብሬ ሳለቅስ በጨለማ ብርሃን ሆንክልኝ
አዝማች · Chorus
መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን
ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰማያዊ ፀዳል ተገርስሶ የተነሳ ቢመስል
ከደብረዘይት መውረድ ልብን ቢያብሰለስል
ጌታ አልተለየኝም አብሮኝ አለ በሸለቆ ሕይወት
የተራሮች አምላክ ብቻ አይደለም አልሰጠኝም ለሞት
አዝማች · Chorus
መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን
ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ