Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ

Egziabhier Bewenet Lemiwedu

5:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ

እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ

እናውቃለን ይሄን እናውቃለን (፬x)

በምድር ሰልፍ ሲያይል ሲበረታ

ያመኑትም ቃልኪዳኑ ሲፈታ

መውጫው ጠፍቶ ቀኑ ሲጨላልም

መባረኪያው ዘመኑ ሲረዝም

ጌታን ታምኖ በአንዳች ሳይጨነቅ

በወጀቡ ፈርቶ ስፍራን ሳይለቅ

ማን ነው እርሱ በእግዚአብሔር ያረፈ

መከራውን በደስታ ያለፈ (፪x)

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ

እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ

እናውቃለን ይሄን እናውቃለን

እናምናለን ይሄን እናምናለን (፫x)

በአንበሶች ጉድጓድ መጣል መርጦ

የአንብን ማስፈራራት ረግጦ

ከልቡ ነው ለአምላክ ያደረሰው

ብርቱ ነፋስ ያላንገዳገደው

አልበላው አውሬው አንደዋዛ

በክብሩ ያ ሰው ተገዛ

ቢመስል እንኳን እግዚአብሔር የጣለው

የሚሆነው ሁሉም ለበጐ ነው (፪x)

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ

እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ

እናውቃለን ይሄን እናውቃለን (፪x)

እንሰብካለን ይሄን እንሰብካለን (፪x)

ቢያሰለችም የምድር ውጣ ውረድ

ሌላው ሲከብር አንተ ብትዋረድ

ብርሃኑ ቶሎ ቢመሽብህ

የታመንከው ድንገት ቢርቅብህ

ያስብሃል ጌታ በሞገሱ

አካሎችህ መከራ እስኪረሱ

አትከፋ በአምላክ ፀጋ ቻለው

አይጥልህም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x)

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ

እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ

እናውቃለን ይሄን እናውቃለን

እንሰብካለን ይሄን እንሰብካለን

እናምናለን ይሄን እናምናለን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ