ይብዛለት ምሥጋና
Yebzalet Mesgana
ትራክ 5 · 4:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይሁን እንጂ ይብዛለት ምሥጋና
ሳላቋርጥ እሰዋለሁ ገና
አይደክመኝም ሁሌ አመልከዋለሁ
ለሕይወቴ ትርጉሟ ኢየሱስ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተሰጥቼ አመልካለሁ በፈቃዴ አመልካለሁ
በመንፈሴ አመልካለሁ በእውነትም አመልካለሁ
በማለዳም አመልካለሁ በቀትርም አመልካለሁ
በምሽትም አመልካለሁ በሌሊትም አመልካለሁ
በዝማሬም አመልካለሁ በሽብሸባም አመልካለሁ
በደስታም አመልካለሁ በዕልልታም አመልካለሁ
አሞጋግሼው መቼ ጨረስኩና
ገና አልጠገብኩም አቅርቤ ምሥጋና
ባማረ ዜማ እቀኝለታለሁ
በገናዬን ይዤ ማልጄ እነሳለሁ
አዝማች · Chorus
አለብኝ ውለታው (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዴት (፬x) እረሳለሁ
እንዴት (፬x) እረሳለሁ
ኧረ እንዴት (፬x) ዝም እላለሁ
እንዴት (፬x) ዝም እላለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የተደረገልኝ ምህረት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው
የተደረገልኝ ቸርነት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው
የተደረገልኝ በጐነት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው
ገና ከፍጥረቴ የቁጣ ልጅ ነበርኩ (፪x)
ምህረት ተደርጐልኝ ከእግዚአብሔር ጋር ታረኩ (፪x)
ያጐበጠኝ ቀንበር ወደቀ ከላዬ (፪x)
አምሮብኝ ብታዩኝ በአምላኬ ዛሬ ቀና ብዬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በኃጥያቴ ሙታን እያለሁ
ከእግዚአብሔር ምረት ተቀብያለሁ
ለሆነው ነገር ምን እከፍላለሁ
ቀንና ሌሊት እዘምራለሁ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
አሞጋግሼው መቼ ጨረስኩና
ገና አልጠገብኩም አቅርቤ ምሥጋና
ባማረ ዜማ እቀኝለታለሁ
በገናዬን ይዤ ማልጄ እነሳለሁ
አዝማች · Chorus
አለብኝ ውለታው (፰x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ተሰጥቼ አመልካለሁ በፈቃዴ አመልካለሁ
በመንፈሴ አመልካለሁ በእውነትም አመልካለሁ
በማለዳም አመልካለሁ በቀትርም አመልካለሁ
በምሽትም አመልካለሁ በሌሊትም አመልካለሁ
በዝማሬም አመልካለሁ በሽብሸባም አመልካለሁ
በደስታም አመልካለሁ በዕልልታም አመልካለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ