አንተን አደንቃለሁ
Anten Adenqalehu
ትራክ 4 · 6:45 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማያትን ሳይ ከዋክብትን
የፀሐይ ድምቀት ግሩም ፍጥረትህ
ምድርን ወብ አድርገህ ማበጃጀትህ
አይጠገብም አቤት ጥበብህ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለአንተ እዘምራለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
አእዋፍ በዛፎች ላይ ተደላድለው ሲያርፉ
በማለዳ መዝሙር ሌሊቱን ሲገልጡ
ብሩህ ልዩ ተስፋ ጥርት ባለው ሰማይ
ትናንት ትናንት አልፎ አዲስ ቀን በቀን ላይ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተን አመልካለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
የፍጥረት ቀለም ድብቅ ውበቱ
የሰማይ ርቀት የምድር ስፋቱ
ግሩም ድንቅ ቤት ለሰው መቆያ
ጌታ ያዘጋጀህ መልካም ማደሪያ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን አመልካለሁ (፫x) ስምረትን እያየሁ
አድማስ ከሩቅ ሆኖ ፍጥረትን ሲታዘብ
ደመና ከሰማይ አውቆ ሲሰበሰብ
በዶፍ ዝናብ መሃል መብረቅ ሲያስተጋብ
ፍጥረት ቤቱን አውቆ በስፍራው ሲገባ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
አንተን አመልካለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ጊዜ ጊዜን ሲወልድ ወቅቱ ሲለዋወጥ
መልካም ፍሬ አበባ አዲስ ዘር ሲገለጥ
ጭጋጉ ደመናው በድንገት ተገፎ
ፀሐይ ስትፈነጥቅ ወቅቱ በወቅት አልፎ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
አንተን አመልካለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
በውድቅት ሌሊት ታይቶ የማይጠገብ
ከዋክብት ሲያበሩ ግርማቸው ሲነበብ
ሰማይ እንደ ድንኳን አምሮ ተዘርግቶ
እንዴት ደስ ያሰኛል ማየት ምድርን ሞልቶ
አዝማች · Chorus
አንተን አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን እያየሁ
ቁጥር 7 · Verse 7
ለአንተ ዘምራለሁ (፪x) አንተን አመልካለሁ ሰማይን እያየሁ
ኦ ሃሌሉያ ኢየሱስ ሥምህ ከፍ ከፍ ይበል
እንደ አንተ ያለ ማን አለ?
ሃሌሉያ!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ