በአንተ ብርታት
Bante Bertat
ትራክ 2 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዴት አልፈዋለሁ ኡሁሁ ኡሁሁ
ያልኩት መከራዬ አሃሃ አሃሃ
እንደ ጠዋት ጤዛ አሃሃ አሃሃ
በነነ ከላዬ (፪x)
የሚያስፈራራኝ ኦሆ ከእግሬ ወደቀ
እንተ ስትመጣ ጌታ ስፍራ ለቀቀ እኮ
አንተ ከሰማይ አሃ አንዴ ካዘዝከው
የማይደነግጥ ኦሆ የማይወድቅ ማን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህን እያሰብኩ ደስ ደስ እያለኝ (፪x)
መከራዬን እረሳሁ ጌታ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፀጥ አለ
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ባሕርም ተከፈለ
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
አልችለውም ያልኩት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ወድቆልኝ አየሁት
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ቁጥር 2 · Verse 2
የሥጋት መንገዴን ኡሁሁ ኡሁሁ
የነፍሴን ሰቆቃ አሃሃ አሃሃ
ዛሬ ተረት ሆነ ኡሁሁ ኡሁሁ
ለቅሶዬም አበቃ (፪x)
እኔም በቀኑ ተራ ደረሰኝ
በክቡር እጅህ ጌታ ክቡር አረከኝ
ያሰፈራራኝን ኦሆ አስፈራራኸው
በምህረትህ ልቤ ደስ አለው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህን እያሰብኩ ደስ ደስ እያለኝ (፪x)
መከራዬን እረሳሁ ጌታ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፀጥ አለ
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ባሕርም ተከፈለ
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
አልችለውም ያልኩት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ወድቆልኝ አየሁት
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ቁጥር 3 · Verse 3
በእኩለ ሌሊት ኡሁሁ ኡሁሁ
ባስፈሪው ጨለማ አሃሃ አሃሃ
ማንም በሌለበት ኡሁሁ ኡሁሁ
ቢጮሁ የሚሰማ (፪x)
ድንገት ተገልጠህ ኦሆ ብርሃን ስትሆነኝ
አስታውሳለሁ ጌታ ሰው ስታደርገኝ
እያሰብኩትም ኦሆ ቸርነትህን አሃ
ዘምረዋለሁ አሃ ምህረትህን (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህን እያሰብኩ ደስ ደስ እያለኝ (፪x)
መከራዬን እረሳሁ ጌታ ስትጐበኘኝ
ወጀቡ ፀጥ አለ
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ባሕርም ተከፈለ
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
አልችለውም ያልኩት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ወድቆልኝ አየሁት
በአንተ ብርታት ጌታዬ በአንተ ብርታት
በአንተ ብርታት አምላኬ በአንተ ብርታት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ