ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
Wetmedu Tesebro Ameletkugn
ትራክ 8 · 5:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል
እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠላቴ ሊያጠፋኝ ሲሸምቅ
የወደኩ መስሎት በእኔ ሊስቅ
ነጋሪት ሲመታ ሲያስመታ
እምነቴን ጉልበቴን ሊፈታ
ቀና ብዬ ባላይ ኖሮ ዓይኖቸን ወደ አንተ አንስቼ
በጠፋሁ ነበር አስካሁን በሰልፉ ብዛት ፈርቼ
ደካማን የምትረዳ አምላክ አኔን ደርሰህ እረዳኸኝ
መከራዬን አሳለፍከው በኮረብታው ላይ አቆምከኝ
አዝማች · Chorus
ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል
እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጠንክሮ ብዙ የፈተነኝ የማይገፋ የመሰለኝ
ወደቀ እንደ ቀላል ዕቃ ሰማሁት ድንፋታው ሲያበቃ
ቀና ብዬ ስመለከት ከመከራዬ ቀን በላይ
ለካስ ጌታ አስቦልኝ ቤቴን በበረከት ሊሞላ
ሸሸገኝ ከጉያው ገባሁ ከጥላው ሥር አሳደረኝ
እዘምራለሁ ለሥሙ በቤቱ ስለተመቸኝ
አዝማች · Chorus
ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል
እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃይሌ ነው እታመነዋለሁ ክብሬ ነው እደገፈዋለሁ
ሞገሴ የማያሳፍረኝ በፀጋው የሚደጋግፈኝ
መከታዬ ነው ጋሻዬ ሥሙን በእውነት እጠራዋለሁ
ስንቱን ሸለቆ ተራራ ከኢየሱስ ጋር አልፌአለሁ
ከጐኔ የሚቆም ዘለዓለም እንዴ እንኳን አላሳፈረኝ
በአምላኬ ቀን ወጥቶልኛል እንግዲህ ማን ሊቃወመኝ
አዝማች · Chorus
ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ
በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ
እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል
እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (፪x)
እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ