ክበር አንተ ብቻ
Keber Ante Becha
ትራክ 1 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኃያላን ከምድር ተሰብረው ሲወድቁ
በራሳችው በትር እራሳቸው ሲያልቁ
አንዱ አንዱን ሲተካው ዓለም ሲለዋወጥ
የጀግና ሰው ዙፋን መንበር ሲገለበጥ
አንተን ግን ጌታ ሆይ ሊደፍር ማን ቻለ
ሥምህ በምድር ላይ እጅጉን አየለ
ብንሰግድልህስ አቤት ያንስብሃል
ጌታ ሆይ ክብርህን በዓይናችን አይተናል
አዝማች · Chorus
ክበር አንተ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፈርዖን ሊያጠፋን ኃይሉን አዘጋጀ
እንዲያው ላይሆንለት ብዙ ጦሩን ፈጀ
አንተ ግን በድንገት ደርሰህ ድል አረከው
ክብር የሚገባው ጌታ ሆይ ለአንተ ነው
ዙፋንህ የፀና ሥምህ የገነነ
ማን አለ እንደ አንተ የተመሰገነ
ብንሰግድልህስ አቤት ያንስብሃል
ጌታ ሆይ ክብርህን በዓይናችን አይተናል
አዝማች · Chorus
ክበር አንተ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሥምህን ሊያጠፉት ብዙዎች ተነሱ
ያለ የሌለውን ጦሩን አስገዝተው
ሽር ጉድ ሲሉ በምድር ጥበብ ዕውቀት
አንተ በሰራኸው ታይተው ሊነግሱበት
አስበው ሲጥሩ ከላይ አየህና
ክብርህስ ሲነካ መቼ ትውድና
ክንድህን ዘርግተህ ገለባበጥካቸው
እንደ ምድር ትቢያ በነነ ሥማቸው
አዝማች · Chorus
ክበር አንተ ብቻ (፫x)
(ይገባሃል) ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ