Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ትልቅ

Egziabhier Teleq

2014 · ትራክ 1 · 6:36 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ችግር ምንድን ነው ከሙላትህ ፊት ሲቆም

ጭንቀት ምንድን ነው ከሰላምህ ፊት ሲቆም

ድካም ምንድን ነው ከጉልበትህ ፊት ሲቆም

ማጣት ምንድን ነው ከዙፋንህ ፊት ሲቆም

ይሟሟሉ ይቀልጣሉ መገኘትህን ሲረዱ

የከበዱት ዙፋን ስጡኝ ያሉ

ለቀው ሄዱ እያፈሩ (፪x)

እግዚአብሔር ትልቅ (፬x)

ከተራራው በላይ ትልቅ

ከከበደው በላይ ትልቅ

ከነገሩኝ በላይ ትልቅ

ከችግሩ በላይ ትልቅ

መንፈስ ቅዱስ ትልቅ (፬x)

ከጨነቀኝ በላይ ትልቅ

ከነገሩኝ በላይ ትልቅ

ከሰበክነው በላይ ትልቅ

ካመለኩት በላይ ትልቅ

የሰልፉ አለቃ ብቻህን ምትገዛ

ምድርን ፍጥረትን በቃልህ ያጸናህ (፪x)

ዕድሜ ማይወጣልህ ኃይልህ አይለካ

ምሽግ መጠለያ ክንድህ የበረታ (፪x)

ገብተህ በእኔ ጓዳ (፪x)

ኧረ ለምን ልፍራ

መንፈስ ቅዱስ ትልቅ (፬)

ከጨነቀኝ በላይ ትልቅ

ከነገሩኝ በላይ ትልቅ

ከሰበክነው በላይ ትልቅ

ካመለኩት በላይ ትልቅ

ምህረትህ ጎትቶኝ ማደሪያህ ገብቼ

እንደሰም እቀልጣለሁ ሸክሜን/ችግሬን እረስቼ (፪)

የፊትህ ብርሀን የህልወናህ ሙቀት

እንደገና አሸንፎኝ ሰመጥኩ/ቀረሁ ባለህበት (፪)

ነፍስም አልቀረልኝ (፪)

ፍቅርህን/እራስህን እፍስሰህብኝ

እግዚያብሔር ትልቅ (፬)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ