Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍፁም ነህ

Fetsum Neh

2014 · ትራክ 3 · 6:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍፁም ነህ ፍፁም በአደራረግህ

ጻድቅ ነህ ጻድቅ በአሰራርህ

መልካም ነህ መልካም በአደራረግህ

ልዩ ነህ ልዩ በአሰራርህ

ወደ ምድረበዳ አባብላታለሁ

ሚስጥሬን ለመግለጽ እኔ እለያታለሁ

ስለኔ ያረግከው ለካ ለበጐ ነው

ስለኔ ያረግከው ለካ በፍቅርህ ነው

ስለኔ ያረግከው ለካ ወደኽኝ ነው

ስለኔ ያረግከው ለካ መርጠኽኝ ነው

ጥያቄ የለኝም መልስ አንተ ሆነኸኝ

በማ እ በሉ ምርሃል መኖር አስለመድኸኝ

ቢያይልም ወጀቡ ቢቆጣም ነፋሱ

ይታዘዛል ሁሉም ለአንተ ለንጉሡ

ለእኔስ ሆኖልኛል ሃይልህን የማይበት

የጠላቴ ወጥመድ ራሱ ሚያዝበት

አብረኸኝ እስከ ሆንክ በመርከበ ላይ

ለመልካም ይሆናል ክብርህን እማይበት

ፍፁም ነህ ፍፁም በአደራረግህ

ጻድቅ ነህ ጻድቅ በአሰራርህ

መልካም ነህ መልካም በአደራረግህ

ልዩ ነህ ልዩ በአሰራርህ

በዓይኖቸ ማየው በፊቴ ያለው

እያንዳንዱን ነገር ፈቅደህለት ነው

በዙፋንህ ሆነህ ትመለከታለህ

ግድ ይለኛል ለኔ ልጄ ነች ትላለህ

እኔ ባይገባኝም ማልፈውን ጐዳና

የምሕረት እጆችህ አቅፈውኛልና

ዛሬም አምንሃለሁ አዎ እንደገና

ነፍሴ አረጋግጣለች ታማኝ ነህ ጌታ

አትተወኝም ጌታ

አንተን ለሚወዱ በአንተ ለተጠሩ

ለበጐ ይሆናል የሚያልፉበት ሁሉ

አትደክም አትተኛ አትዝል አትረሳ

ታውቀሃል እንደሆንክ መልካሙ እረኛ

በበትህ የኖረ በአንተ የተመካ

አያፍርም ዘለዓለም ለአንድም ደቂቃ

ግን አስቀምጠኸው ከአብ ጋር በከፍታ

ከሞገስህ ጠግቦ ይኖራል በግርማ

ፍፁም ነህ ፍፁም በአደራረግህ

ጻድቅ ነህ ጻድቅ በአሰራርህ

መልካም ነህ መልካም በአደራረግህ

ልዩ ነህ ልዩ በአሰራርህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ