ይገርመኛል
Yegermegnal
2014 · ትራክ 9 · 7:12 · አማርኛ
ኦ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
በእናቴ ማህጽን ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ኧረ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
ገና በሃጥያቴ ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
እሮጥኩኝ እሮጥኩኝ ለብዙ ዘመን
ፍቅርን የማገኘው በልፋት መስሎኝ
ዝም አልከኝ እስክመጣ ድክሞኝ በቅቶኝ
እጄን እስክሰጥህ መፍትሄ ጠፍቶኝ
ታገስከኝ ልትለኝ
እኔ ነኝ የማነጻሽ ወደሃሳቤ ምመልስሽ
እኔ ነኝ የመረጥኩሽ ወደ እራሴ የምስብሽ
እኔ ነኝ የምለይሽ በፍቃዴ የማስኬድሽ
ኦ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
በእናቴ ማህጸን ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ኧረ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
ገና በሃጥያቴ ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ሃሳቤን በሙሉ ከሩቅ ታውቀዋለህ
የሥጋዬን ድክመት አዎ ታየዋለህ
የለኝም ማቀርበው ከእኔ የሆነ
በቅድስና ውስጥ ለመቆም የቻለ
ግን ኢየሱስ አለ ሚያስገባኝ ወደ አንተ
ሊቀ ካህን ለዘለዓለም
የሚሽረው አንዳችም የለም X፪
በአንተ ፊት ሚማልድልኝ
እንዳልጠፋ የሚዋጋልኝ
ኦ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
በእናቴ ማህጽን ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ኧረ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
ገና በሃጥያቴ ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
በጨለማ ብሆን አንተ ብርሃኔ ነህ
መንገዴንም ብስት ትመልሰኛለህ
አልፈቀድክለትም ከሳሼ እንዲቀጥል
ቀደህ እስክታስወግድ የጥፋቴን ዝርዝር
ከፍለህ ዋጋዬ የሃጥያት እዳዬን
አስታረከኝ ከአባቴ ጋራ
በሰራኸው የመስቀል ስራ X፪
ወደኸኛል ገና ሳላውቅህ
ይደንቀኛል ኢየሱስ ፍቅርህ
ኦ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
በእናቴ ማህጽን ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ኧረ እኔስ ይገርመኛል
እኔስ ይደንቀኛል
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ X፪
ገና በሃጥያቴ ሳለሁ
በፍቅር ዓይኖችህ ታየሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ