አምንሃለሁ
Amnehalehu
2014 · ትራክ 5 · 6:57 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይገባኝም ፊቴ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይሞላም በእጄ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይመስለኝም ፊቴ ያለው
እኔ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ብቻ አንተ ክበር እጄ ባለው
ቁጥር 1 · Verse 1
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የታዘዘውን
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የተላከውን
ይታለፋል ይታለፋል ነገር ሁሉ
እንዳልነበር እንዳልሆነ በቀላሉ
ባንተ ብርታት ባንተ ጉልበት ለተመኩ
መንገድ አለ መውጫ አለ ከወጥመዱ
አይቻለው አጥንቶቼን ስታበረታ
በሞተው ነገር ላይ ህይወትን ስትዘራ
ለፃድቅ ነህ በክፉ ቀን መጠለያ
የፀና ግንብ ላመኑብህ ኦ መከታ
አዝማች · Chorus
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይገባኝም ፊቴ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይሞላም በእጄ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይመስለኝም ፊቴ ያለው
እኔ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ብቻ አንተ ክበር እጄ ባለው
ቁጥር 2 · Verse 2
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የታዘዘውን
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የተላከውን
አንተ አይደለህ በዘመናት የታወከው
በመልካምነትህ ህዝቡን ፀጥ ያረከው
ባይመሰክር አፉን ከፍቶ ስጋ ለባሽ
ድንጋይ ወንዙ ይናገራል ነህ አባት
ታማኝነትህ ተፈትኖ የፀና
አትለወጥ አትደክም የሁሉ ጌታ
አልተገኘም አይገኝም አንተን ሚተካ
ብቻህን ነህ ለፍጥረት ሁሉ ከለላ
አዝማች · Chorus
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይገባኝም ፊቴ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይሞላም በእጄ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይመስለኝም ፊቴ ያለው
እኔ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ብቻ አንተ ክበር እጄ ባለው
ቁጥር 3 · Verse 3
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የታዘዘውን
ቃልህ ካፍህ ወጥቶ መች ተመልሷል
ሳያደርግ ሳይፅም የተላከውን
አንዳንዶቹ በሰረገላቸው ሲመኩ
ሌሎች ደግሞ ብዛታቸውን ሲቆጥሩ
ሁሉም ይኸው በየተራ እንዲያው አለፉ
አንተ ግን ያው እንዳማረብህ ክርህን አልነኩ
ምክር ትዕዛዝህ የፀና ለዘለአለም
ከአፍህ ቃል አንዳች እንኳን የሚወድቅ የለም
ትደምቃለህ ትከብራለህ ገና ገና
መች ቀመስነው መች አየነው ያንተን ግርማ
አዝማች · Chorus
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይገባኝም ፊቴ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይሞላም በእጄ ያለው
አምንሃለሁ አምንሃለሁ ባይመስለኝም ፊቴ ያለው
እኔ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ብቻ አንተ ክበር እጄ ባለው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ