ፍቅር ማለት
Feqer Malet
2014 · ትራክ 6 · 4:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አልሳሳ በልጅህ ሲመጣ
አልቀስ የቁጣህን መጠን
እኔ ላጠፋሁት ክፉ ላደረኩት
ሰዋኸው ቅዱሱን ሃጥያት ያላየውን
የዓለም ፍርድን ሲወስድ
ፊትህን ያዞርከው
አስበኸኝ ነው ወደኸኝ ነው
መርጠኸኝ ነው አውቀኸኝ ነው
ራርተህልኝ ነው አዝነህልኝ ነው
ሳስተህልኝ ነው አፍቅረኸኝ ነው
አዝማች · Chorus
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ብቻህን ፍቅር ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ደግ ነህ ክፉ ላሰበብህ
ትራራለህ ልቡን ላዞረብህ
እየዘበቱብህ እያሾፉብህ
ስራቸውን አያውቁም የሚያደርጉትን
ምሕረት አርግላቸው ብለህ የጸለይክ
ልዩ ነህ የተለየህ
አቤቱ ፍቅርህ አቤት ምሕረትህ
ውብ ነህ የተለየህ
አቤት በጐነትህ አቤቱ ፍቅርህ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ብቻህን ፍቅር ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ምሕረትህ ለዓለም ሁሉ
አዲስ ነው በየጥዋቱ
ሃጥያትን ለሰሩ ለበደሉ
እጅህ ይዘረጋል ለያንዳንዱ
የትላንቱን እረስተህ እንዳጠፉ
ምሕረትህ ብዙ በጐነትህ ብዙ
ፍቅርህ ብዙ ቸርነትህ ብዙ
ትህትናህ ብዙ ርህራሄህ ብዙ
ትዕግሥትህ ብዙ መውደድህ ብዙ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ፍቅር ማለት አንተ ነሀ
ሲጀመርም ሲጨረስ
ብቻህን ፍቅር ነህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ