እንደሰው አይደለም
Endesew Aydelem
ትራክ 5 · 5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንደ ሰው አይደለም እርሱ ሁሉን ይችላል
እንደ ሰው አይደለም እርሱ ሁሉን ይችላላ
እንደ ሰው አይደለም እግዚአብሔር ሁሉን ይችላል
እንደ ሰው አይደለም እግዚአብሔር ሁሉን ይችላላል
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃጥያትን እግዚአብሔር ይቅር ይላል
ከዓመጻም እርሱ ያነጻል
ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው
ምህረቱ ግን ለዘለዓለም ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ይሁን ያለው ይሆናል
ምድርና ሞላዋን እርሱ ፈጥራል
ለእግዚአብሔር የለም የሚሳነው
ኤልሻዳይ አምላክ ሁሉን ችይ ነው
በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ
አንዳች የማይታጣው ነው ብርቱ
እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው
አይደክምም እርሱ አይታክትም
ማስተዋሉም አይመረመርም
ቁጥር 3 · Verse 3
እርሱ እግዚአብሔር ፊተኛ ነው
በኋለኞችም ዘንድ የሚኖር ነው
የእስራኤል ፈጣሪ ቅዱስ ነው
እግዚአብሔር እርሱ ንጉሥ ነው
ሥልጣን አለው ይምራል ይፈረዳል
ያነሳል ይሾማል ያከብራል
ለሰው የማይቻል ለእርሱ ይቻላል
እግዚአብሔር ሁሉ ይቻለዋል
ይራራል ይወዳል ይባርካል
ይጠራል ይለያል ይልካል
ቁጥር 4 · Verse 4
ከእርሱ በፊት አምላክ አልነበረም
ከእርሱ በኋላም ማንም ዓይኖርም
እግዚአብሔር እርሱ እግዚአብሔር ነው
የሚያድን አምላክ እርሱ ብቻ ነው
ያደርጋል በባሕር ውስጥ መንገድን
በኃይለኛ ውኃ ውስጥ መተላለፊያን
ይዋጋል ይረታል ያሸንፋል
በዙፋኑ ዘለዓለም ይኖራል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ