ሃሌሉያ
Hallelujah
ትራክ 4 · 4:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬ ከፍ ከፍ አድርግሃለሁ
ስምህን ለዘላላም እባርካለሁ
እጅግ የተመሰግንህ እግዚአብሔር ታላቅ ነህ
ለታላቅነትህ ፍጻሜ የሌለው
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ርህሩህና መሐሪ ነው
ከቁጣ የራቀ ምህረቱ ብዙ ነው
ለሚታገሱት እርሱ እግዚአብሔር ቸር ነው
ምህረቱ ያምላካችን በስራው ሁሉ ላይ ነው
በቃሎችህ አቤቱ አንተ ታማኝ ነህ
በስራህም በመንግድህ ሁሉ ጽድቅ ነህ
ተስፋ ለሚያደርጉህ ሁሉ አንተ እጅህን ትከፍታለህ
ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ
አዝማች · Chorus
መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት
እግዚአብሔር ለልጅ ልጅ ነው የአንተ ግዛት
አቤቱ ስራህ ሁሉ አንተን ያመስግኑሃል
ቅዱሳንህም ሁሉ አንተኑ ይባርኩሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ