ምሥጋና
Mesgana
ትራክ 8 · 5:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ለአንተ ምሥጋና
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ለአንተ ምሥጋና
ዝማሬ ዝማሬ ዝማሬ ለአንተ ዝማሬ
ሙገሳ ሙገሳ ሙገሳ ለአንተ ሙገሳ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማየ ሰማያት ለአግዚአብሐር ምሥጋና
በአርያምም ለእግዚአብሔር ምሥጋና
ሰራዊቱ ሁሉ ጌታን አመስግኑት
ጽሀይና ጨረቃም እርሱን አመስግኑት
ክዋክብትና ብርሃን እርሱን አመስግኑት
የሰማያት በላይ ውሃም አመስግኑት
እርሱ ብሏልና ሁኑ እነርሱም
እርሱ አዞአልና ተፈጠሩም
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ እግዚአብሔር ይመስግን
እግዚአብሔርን ከሰማይ አመስግኑት
እግዜአብሔርን ከምድር አመስግኑት
የእግዚአብሔርን ስሙን አመስግኑት
ቁጥር 2 · Verse 2
የምድር ነገሥታት አህዛብም ሁሉ
አለቆችና ፈራጆች ሁሉ
ጐማሶችና ቆነጃጅቶች
አመስግኑት ሽማግሌዎች ልጆች
ሥሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏል
ምሥጋናው በሰማይ እና በምድር ሆኗል
የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል
ለእግዚአብሔር ሥም ምሥጋና ይገባል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ