Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ና ወንድሜ

Na Wendemie

ትራክ 9 · 5:49 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ና ወንድሜ ና ወደ ጌታ ኢየሱስ ና

ነይ እህቴ ነይ ወደ ጌታ ኢየሱስ ነይ

ና ወንድሜ ያሳርፍህ ሸክምህን ያወርድልህ

ሸክምህን ያውርድልህ

ነይ እህቴ ያሳርፍሽ ሸከምሽን ያውርድልሽ

የተጨነቅህ ሸክም የከበደህ

ና ኢየሱስ ያጽናናህ ያሳርፍህ

የተጠጨነቅሽ ሸክም የከበደሽ

ነይ ኢየሱስ ያጽናናሽ ያሳርፍሽ

በሃጥያት ውስጥ ያለህ የጨለመብህ

ና ኢየሱስ ያድንህ ብርሃኑን ያብራልህ

በሃጥያት ውስጥ ያለሽ የጨለመብሽ

ነይ ኢየሱስ ያድንሽ ብርሃኑን ያብራልሽ

ተስፋ የቆረጥህ ኑሮ የመረረህ

ና ኢየሱስ ያድስሽ ኑሮን ያጣፍጥልሽ

ተስፋ የቆረጥሽ ኑሮ የመረረሽ

ነይ ኢየሱስ ያድስሽ ኑሮን ያጣፍጥልሽ

ወደ ሲኦል ሳትሄድ ሳይቀድምህ ሞት

ና ኢየሱስ ይስጥህ የዘለዓለም ሕይወት

ወደ ሲኦል ስትሄጅ ሳይቀድምሽ ሞት

ነይ ኢየሱስ ይስጥሽ የዘለዓለም ሕይወት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ