የሚመስልህ የለም
Yemimesleh Yelem
ትራክ 2 · 5:45 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሚመስልህ የለም አንተ እግዚአብሔር ነህ
የሚመስልህ የለም አንተ ድንቅ ነህ
የሚመስልህ የለም አንተ እግዚአብሔር ነህ
የሚመስልህ የለም አንተ ልዩ ነህ
ምህረትህ ብዙ ነው ከሕይወት ይሻላል
ፍቅርህም ጥልቅ ነው እንደሞት ይበረታል
ትዕግሥትህ ታላቅ ነው ዘመናት ያልፋል
እግዚአብሔር ድንቅ ነህ ማን ይመስልሃል
በዘለዓለም ዙፋን በክብር ተቀምጠሃል
እግዚአብሔር ብርሃን ነህ ብርሃንን ለበሰሃል
በቃልህ ሰማይን ምድር ፈጥረሃል
ኤልሻዳይ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃል
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ አንተ ብቻ ነህ
ምድርና ሞላዋን ተመለከታለህ
ከቅዱስ ማደሪያ ትህዛዝ ትሰጣለህ
ፍጥረትን በሙሉ አንተ ትገዛላህ
ሰማይት ክብርህን ይናገራሉ
ፍጥረታት በሙሉ ድምጽህን ይሰማሉ
ለቃልህ በፍርሃት ይታዘዛሉ
ክብርን በሙሉ ለአንተ ያመጣሉ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አንተ የለም የሚመስልህ
እጅግ ከፍ ያልክ ነህ በግርማ ሞገስህ
ሰው በኢየሱስ ብቻ አንተን ይቀርብሃል
በእውነት በመንፈስ ደግሞ ይሰግድልሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ