ትሁቱ ከአንተ ልማር
Tehutu Kante lemar
ትራክ 10 · 6:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳ ሁለ ወደ እኔ ኑ
እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ
እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና (የማቲዎስ ወንጌል ምህራፍ ፲፩ ፳፮ ፴)
አዝማች · Chorus
ያላሸከመከኝን እንዳልሸከም
ከብዶኝ አንገዳግኝ እንዳልደክም
ያላሳየኸኝን አይቼ
እንዳልቆም ግራ ተጋብቼ
ያልሰጠኸኝንም ወስጄ
እንዳልቀር ኋላ ባዶ እጄን
የላደረከኝንም ሆኜ
እንዳልቀል በአንተ ተመዝኜ
አዝማች · Chorus
ትሁቱ ከአንተ መማር እፈልጋለሁ
ታዘኸውን እግዚአብሔርን ደስ እንዳስኘኸው
ትሁቱ ከአንተ መማር እፈልጋለሁ
ታዘኸውን እግዚአብሔርን ደስ እንዳስኘኸው
ቁጥር 2 · Verse 2
አስተምረኝ ኢየሱስ መንገድህን
አንተን ተክትዬ መራመድን
እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ
እሺ አስተምረኝ አንተ እንደፈልክ
ቁጥር 3 · Verse 3
ስታዘኝ ሳልታዘዝህ ቀርቼ
እንዳልገኝ ለጠላቴ ተመችቼ
ስጠራኝ ድምጽህን ሳላውቀው ለይቼ
እንዳልጠፋ በክፉው እጅ ተነድቼ
ባስቀመጥከኝ በስፍራዬ ሳልቀመጥ
እንዳታጣኝ በቦታዬ ስትገለጥ
በሰጠኸኝ በመክሊቴ ሳላፈራ
እንዳትመጣብኝ የአንተን ስራ ሳልሰራ
በፈቃዴ በስሜቴ እየኖርኩኝ
ጌታ እንዳልስት የአንተ ፈቃድ ነው እያልኩኝ
የቆምኩኝ መስሎኝ ሳልቆም የቀረሁ እንዳልሆን
እንዳልወድቅ ኋላ ልጠንቀቅ አሁን
አለሁ እያልኩኝ በቤትህም እኖራለሁ
ውጭ እንዳልሆን ጌታ ሆይ እፈራለሁ
አዝማች · Chorus
ዛሬ ብገኝ በአንተ ወደ አምላክ ቀርቤ
እንዳልዘነጋው በአንተ መሆኑን መታሰቤ
ትሁት የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ
ልዝብ ነው በእርሱ ማረስ እቻላለሁ
ትሁት የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ
ልዝብ ነው በእርሱ ማረስ እቻላለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን ተክትዬ መራመድን
እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ
እሺ አስተመረኝ አንተ እንደፈልክ
አንተ ምራኝ አንተው መዳን እንደሆንከኝ
ፍጻሜዬን አንተው አሳምርልኝ
እንዳረከኝ ብቻ እንዳልከኝ አድርገኝ
ሁልጊዜ በአንተ ውስጥ ኢየሱስ ሰውረኝ
አንተ እዘዘኝ አንተ ብቻ በኔ ስራ
እኔም ከፈቃድህ ልስማማ ከአንተ ጋራ
ይስማማኛል ልዝብ ነው ቀንበርህ
አሸከመኝ ቀሊል ነው የአንተ ሸክምህ
አዝማች · Chorus
ትሁቱ የአንተን ሸክም እሸከማለሁ
ቀሊል ነው በእርሱ መሄን እችላለሁ
ትሁት የአንተን ሸክም እሸከማለሁ
ቀሊል ነው በእርሱ ማሄድ እችላለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
አስተምረኝ ኢየሱስ መንገድህን
አንተን ተክትዬ መራመድን
እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ
እሺ አስተመረኝ አንተ እንደፈልክ
ቁጥር 6 · Verse 6
አያስኬድም ሌላው ፈጽሞ አይመችም
የሚያስቆም ነው ወደፊት አያራምድም
አይስማማም ፍፁም አይሰጥም ደስታ
ባዶነት ነው ከንቱ ያለ አንተ ጌታ
ማትረፍ የለም መክሰር ነው በጉዞዬ
የለአንተ ግቡ አይደርሥም አላማዬ
እንተ እንዳልክ ከአንተ መማርን መርጣለሁ
ስታደርገው እያየሁ አከብርሃለሁ
ትሁቱ ከአንተ ልማር እሺ እላላሁ
በአንተ ላይ አርፌ መጉዋዝን እሻለሁ
አዝማች · Chorus
ትሁቱ የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ
ልዝህብ ነው በእርሱ ማረስ እችላለሁ
ትሁቱ የአንተን ሸክም እሸከማለሁ
ቀሊል ነው በእርሱ መሄድ እችላለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ