ጌታ ኢየሱስ
Gieta Eyesus
ትራክ 1 · 6:09 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
የሰማይ የምድር ንጉሥ
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ
የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ
ሥሙ ክብር አለው
ሥሙ ክብር አለው
ሥሙ ክብር አለው
ሥሙ ክብር አለው
ቁጥር 1 · Verse 1
ከመጀመሪያው ያለ የሁሉ መሰረት የሆነ
በሰማይም በምድርም ሥሙ እጅግ የገነነ
በእግዚአብሔር መላዕክቶች ፊት ታማኝ ነው የከበረ
ዙፋኑ ዘለዓለማዊ በቅድስናው ያማረ
ቁጥር 2 · Verse 2
በእግዚአብሔር መላዕክቶች ፊት ታማኝ ነው የከበረ
ዙፋኑ ዘለዓለማዊ በቅድስናው ያማረ
ቁጥር 3 · Verse 3
በወርቅ መቅረዞች መሃል በክብር ያሚመላለስ
ድምጹ እንደ ብዙ ውሃዎች ድምጽ እግሮቹ እንደነጠረ ናስ
ደረቱን በወርቅ ታጥቋል ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል
ከአፉ ስይፍ ይወጣል ፊቱ አንደ ፀሐይ ያበራል
ቁጥር 4 · Verse 4
ደረቱን በወርቅ ታጥቋል ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል
ከአፉ ስይፍ ይወጣል ፊቱ አንደ ፀሐይ ያበራል
ቁጥር 5 · Verse 5
መጽሐፊንፉንም ሊወሰድ መሐተሞቹን ሊፈታ
የገባዋል ኢየሱስ የጌቴች ሁሉ ጌታ
ለእግዚአብሔር አዲስ ሕዝብን በደሙ ስለዋጀ
መንግሥትና ካህናት ለአምላኩ አዘጋጀ
ቁጥር 6 · Verse 6
ለእግዚአብሔር አዲስ ሕዝብን በደሙ ስለዋጀ
መንግሥትና ካህናት ለአምላኩ አዘጋጀ
ቁጥር 7 · Verse 7
ለወደደን በደሙ ከኃጢአታችን ላጠበን
ለአምላኩ መንግሥትና ካህናት ላደረገን
በክብር ለሚመጣው ኃይል ለእርሱ ይሁን
እሰከዘለዓለም ድረስ ክብርም ለእርሱ ይሁን
አዝማች · Chorus
በክብር ለሚመጣው ኃይል ለእርሱ ይሁን
እሰከዘለዓለም ድረስ ክብርም ለእርሱ ይሁን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ