ኢየሱስ ቤቴ ገባ
Eyesus Bietie Geba
2013 · ትራክ 8 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔን የሚገርመኝ እግዚአብሔር ነው
የፍቅሩ ብዛት እንዴት ድንቅ ነው (፪x)
የከበረ ነገር ከእርሱ ይፈልቃል
ተስፋ ያጣውን ሰው ሞገስ ያገኘዋል
ምስኪን ምጻተኛ አሃ አሃ አቅም ያነሰዉ
የኢየሱስ ደግነት አሃ አሃ ሰላም ወረሰዉ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ነገሬን ቀየረው ቀያየረው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ህመሜን ከላዬ በፍቅሩ አከመው
የደከመ ሕይወቴን በቃሉ ፈወሰው
ፈጥኖ ተመለሰ የነፍሴ እርካታ/ደስታ
እስኪ ለጌታዬ ልቅረብ/አምጡልኝ በምሥጋና (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ነገሬን ቀየረው ቀያየረው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዓይኖቼ ሲቀኑ ጌታ ወዳለበት
ጠል ከላይ ወረደ አባቴ ካለበት
በትዝታ መኖር አሃ አሃ ጠፋ ከሕይወቴ
ፈጥኖ ሲሆንልኝ አሃ አሃ ሠማይ እረዳቴ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ነገሬን ቀየረው ቀያየረው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ኢየሱስ ቤቴ ገባ (፪x)
አባ ቤቴ ገባ
ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው
ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ብቻዬን ትቶኝ አልሄደም ጌታዬ ፣ ጌታዬ
ለብቻዬ ትቶኝ አልሄደም ወዳጄ ፣ ወዳጄ
ለአንድ አፍታ ትቶኝ አልሄደም ጌታዬ ፣ ጌታዬ
ብቻዬን ትቶኝ አልሄደም ወዳጄ ፣ ወዳጄ (፪x)
ጌታዬ ባለውለታዬ (፯x)
አንተ ብቻ . (1) .
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ