Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ነገን አያለሁ

Negen Ayalehu

2013 · ትራክ 2 · 5:11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሕይወቴ ዘመን ሰላም ያገኘሁት

ጻዲቁን ሳምን ነው የተረጋጋሁት

የቀድሞ ታሪኬ እንደዚህ አልነበረም

በናዝሬቱ ኢየሱስ ሕይወቴ አማረ

ዛሬ ላይ ሆኜ ነገን አያለሁ

ተስፋን የሰጠኝ የታመነ ነው

አላሻግርም ብሎ ያስቸገረ

በጌታ ኢየሱስ ተሰብሮ ታየ

እግዚአብሔር ወዳጄ የዘለዓለም ወዳጄ (፫x)

እግዚአብሔር ሰላሜ የዘለዓለም ሰላሜ (፫x)

እግዚአብሔር እረፍቴ የዘለዓለም እረፍቴ (፫x)

እግዚአብሔር ወዳጄ የዘለዓለም ወዳጄ (፫x)

እግዚአብሔር ሰላሜ የዘለዓለም ሰላሜ (፫x)

እግዚአብሔር እረፍቴ የዘለዓለም እረፍቴ (፫x)

(ሰላሜ እረፍቴ ወዳጄ የዘለዓለም ወዳጄ)

ዘመድ አልባ ሕይወት በኢየሱስ ሲተካ

አስገራሚ ውህደት ሰላም አለው ለካ

በተስፋ ያማረ ሕይወት አግኝቻለሁ

በለመለመው መስክ መኖር ጀምሪያለሁ

ዛሬ ላይ ሆኜ ነገን አያለሁ

ተስፋን የሰጠኝ የታመነ ነው

አላሻግርም ብሎ ያስቸገረ

በጌታ ኢየሱስ ተሰብሮ ታየ

እግዚአብሔር ወዳጄ የዘለዓለም ወዳጄ (፫x)

እግዚአብሔር ሰላሜ የዘለዓለም ሰላሜ (፫x)

እግዚአብሔር እረፍቴ የዘለዓለም እረፍቴ (፫x)

እግዚአብሔር ወዳጄ የዘለዓለም ወዳጄ (፫x)

እግዚአብሔር ሰላሜ የዘለዓለም ሰላሜ (፫x)

እግዚአብሔር እረፍቴ የዘለዓለም እረፍቴ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ