Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምን እልሃለሁ

Men Elehalehu

2013 · ትራክ 7 · 5:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደ ሲና ምድር እንደ በረሃዉ

ጠል ከእርሱ እርቆ . (1) .

ትካዜ ሰፍኖበት ሆኖ ረዳት አልባ

እንዲህ ያለው ምስኪን ልምላሜን ሰማ

አሄ ልምላሜን ሰማ

ምን እልሃለው (፫x)

ከእግርህ ሥር ወድቄ አመሰግናለው (፪x)

ብቸኝነት ዓለም ወግ ሆኖ በሕይወቴ

አጠገቤ ነበር ለካስ ደጉ አባቴ

ቅርበቱን አወኩት ድምጹንም ሰማሁት

እንደ ብዙ ወዳጅ ሆኖ አገኘሁት

አሄ ሆኖ አገኘሁት

ያንን የጭንቅ ቀን የብቸኝነቴን

ክንድህ ባይረዳኝ ፀጋህ ባያግዘኝ

ኧረ እኔስ የት ነበርኩኝ (፪x)

እናት አባት ዘመድ ለእኔስ ኢየሱሴ ነው

ቀን ከሌት ስራመድ ልቤ የሚያስበው

በኛ ክፉ ቀናት ረዳት በሌላቸው

መጽናናት ሆነልኝ ዳስሼው ነክቼው

አሄ ዳስሼው ነክቼው

ምን እልሃለው (፫x)

ከእግርህ ሥር ወድቄ አመሰግናለው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ