አልረሳም
Alresam
2013 · ትራክ 12 · 6:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አልረሳም አልረሳም አልረሳም
ጌታ ውለታህን አልረሳም
ከአፈር ከትቢያ ላይ ሲያነሳኝ
ለወግ ለማዕረግ ሲያበቃኝ
አልረሳም እኔስ አልረሳም
አልረሳም እኔስ አልረሳም (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅሩን አልረሳም ምህረቱን አልረሳም
ችሎታውን አልረሳም ያረገውን አልረሳም
ያባትነትህን ክብርህን አይቻለሁ
ከአንተ የተነሳ እዚህ ደርሻለሁ
ለነገ ሚያስፈራኝ ሚያሰጋኝ የለኝም
አምላኬ ዘለዓለም ከፍ በልልኝ
ከፍ ከፍ በልልኝ
አንተው ከፍ በልልኝ
ከፍ ከፍ ከፍ በልልኝ
አባው ከፍ በልልኝ
ከፍ ከፍ ከፍ በልልኝ
ከፍ ከፍ በልልኝ
ከፍ በልልኝ
አንተው ከፍ
ቁጥር 2 · Verse 2
እስኪ ማነው የደሃ አደጉ አባት
ኧረ እስኪ ማነው ለምስኪኑ ደራሽ
ኧረ እስኪ ማነው የመበለት ዳኛ
ኧረ እስኪ ማነው ለተጠቃው ፈራጅ
እስኪ ማነው ከአምላኬ በቀር
እስኪ ማነው ከውዴ በቀር
ኧረ እስኪ ማነው ከኢየሱስ በቀር
እስኪ ማነው ከአባቴ በቀር
እስኪ ማነው ከአምላኬ በቀር
እስኪ ማነው ከውዴ በቀር
እስኪ ማነው ከኢየሱስ በቀር
እስኪ ማነው ከአባቴ በቀር
ቁጥር 3 · Verse 3
ለማን ተደረገ ለማንስ ሆነ
ለእኔ የሆንከውን እንዴት ልርሳው (፪x)
ለማን ተደረገ ለማንስ ሆነ
ለእኔ የሆንከውን እንዴት ልርሳው (፪x)
እስኪ ላምጣ ላቅርብ ሙሉ ክብር
አንተ እኮ ክብሬ ነህ እንዴት ዝም ልበል
ውርደቴን በክብር ለውጠህ አይቻለሁ
ከሰው የተለየ ምሥጋናን ይዣለሁ
አዝማች · Chorus
እኔስ አልረሳም ፍቅሩን አልረሳም
እኔስ አልረሳም አልረሳም
እኔስ አልረሳም አልረሳውም
እኔስ አልረሳም ፍቅሩን አልረሳም
እኔስ አልረሳም ምህረቱን አልረሳም
እኔስ አልረሳም ችሎታውን አልረሳም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ