አልሻም
Alesham
2013 · ትራክ 5 · 5:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በረሃብ ቀጠና አይደለሁም እኔ
ልምላሜ ረግፎ አልገደለኝ ጠኔ
በአረንጓዴው ገነት ምንጭ በሚፈልቅበት
እንድኖር ተፈርዷል በኢየሱስ ዳኝነት
አዝማች · Chorus
አልሻም ከአንተ ውጭ ብልጭልጩን ዓለም
ቁጥር 2 · Verse 2
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም (፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
ለምንድን ነው አሉኝ ክርስትያን የሆንከው
ሁልጊዜ ኢየሱስ ኢየሱስ ምትለው
እስቲ ልንገራችሁ ይህንን ሚስጥር
. (2) . አይሎ ነው የመስቀሉ ፍቅር
አዝማች · Chorus
አልሻም ከአንተ/ከእርሱ ውጭ ብልጭልጩን ዓለም
ቁጥር 3 · Verse 3
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም (፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
ነፍሴ አዋጅ ሰምታ የሞትን ቀጠሮ
ፍጥረት ሲያወራ የሽንፈት እሮሮ
ሕይወት ያበዛልኝ ማነው ከተባለ
አዳኙ ኢየሱስ ነው በዙፋኑ ያለ
አዝማች · Chorus
አልሻም ከእርሱ ውጭ ብልጭልጩን ዓለም
ቁጥር 4 · Verse 4
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም (፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
እስግዲህ በኢየሱስ ተደላድያለሁ
ዓለም የማይሰጠውን ሰላም አግኝቻለሁ
ታዲያ ለምን ልሩጥ ለምን ልቅበዝበዝ
እስቲ በኢየሱስ ላይ እርፍ ልበል
እርፍ እርፍ እርፍ እርፍ ድግፍ
ጥግት ጥግት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ