ማራናታ
Maranatha
2013 · ትራክ 13 · 5:01 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አስሩ ቆነጃጅቶች ሙሽራውን ሲጠብቁ
አምስቱ ልባሞች ነበሩ
አምስቱ ደግሞ ሰነፎች
ታዲያ አንተ ከየትኛው ነህ
አንቺስ እህቴ ሆይ
ሙሽራው በደጅ ነው
ለኩስ ኩራዝህን ለኩሽ ኩራዝሽን
አዝማች · Chorus
ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ናፍቆታችን አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
ማራናታ (ቶሎ ና) አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
የዚህ ዓለም መከራ እጅግ ቢበረታ
ሙሽራው በደጅ ነው ሊመጣ
እስኪ እንበል ማራናታ
አዝማች · Chorus
ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
ቁጥር 3 · Verse 3
ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
ሙሽራ ሆይ ቶሎ ና ቶሎ ና
ሙሽራ ሆይ ቶሎ ና (፬x)
እረፍት የተጠራ እንደኛ ማነው
በምድር ተቀምጦ በሠማይ ርስት ያለው (ርስት ያለው (፪x))
እንሄዳለን አዲሲቱ ሃገር (ሃገር ሃገር ሃገር አለኝ)
አገር አለኝ በሠማይ (በሠማይ)
ከበጉ ጋር በደስታ ልንኖር (ልንኖር)
ሙሽራው ሊመጣ በደጅ ነው (በደጅ ነው (፪x))
በደጅ ነው በደጅ ነው (በደጅ ነው)
ቁጥር 4 · Verse 4
ማራናታ (ቶሎ ና ቶሎ ና)
ቁጥር 5 · Verse 5
አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ