ገናና
Genana
2018 · ትራክ 4 · 4:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ በስራህ - ስምህ የገነነ
በሰማይ በምድር - የተመሰገነ፤
ያንተን ህልውና - የሚጠራጠሩ
በእጆችህ ስራ - ከምክንያት አጠሩ
ገናና ነህ ዝነኛ
የፍጥረት ምንጩ መገኛ
ጅማሬህን አናውቀው - ፍፃሜህን አናውቀው
በ'ድሜያችን በምናውቅህ - ስራህን እናድንቀው!
ጥበብህ ሰላምህ - ላ'ለም የሚበቃ
ድንቅ፥ መካር፥ ኃያል - የሰላም አለቃ፤
መላእክት ባንድ ላይ - ቅዱስ ነህ ይሉሃል
የለም የሚመስልህ - ከሚኖሩት መሃል
አዝማች · Chorus
አዝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ባ'ንተ ያለን ሞኝነት - ከእውቀት ሚዛን ቢጣል
ባ'ለም ካሉ ጥበቦች - ብዙ ርቀት ይበልጣል፤
ያ'ንተ ስራ ሲታወጅ - በምድር ላለ አካል
ምስጋናህ በህዝብህ ላይ - እንዳ'በባ ይፈካል
አዝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ስ'ሰጠን ተመስገን፥ ስታስቀር ተመስገን
ያልነውን ነው እንጂ - ያልከውን አትነፍገን፤
ከምናውቅህ በላይ - ስምህ ከፍ ያለ ነው
አፍረንብት አናውቅም - አንድ ጊዜም ጠርተነው
በክብርህ የመጡን - እግዚአብሔር ተዋጊ
ከቤትህ የጠፉን - እግዚአብሔር ፈላጊ፤
እግዚአብሔር ኃይለኛ - እግዚአብሔር ከፍታ
እግዚአብሔር አምባችን - እግዚአብሔር መከታ!
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር - እግዚአብሔር
እግዚአብሔር አንተን ነው - ዘውትር የምንጠራው
የትኛው ጀግና ነው - አንተን የሚያስፈራው!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ