Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሌሉያ

Hallelujah

2012 · ትራክ 10 · 7:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በምድር ላይ ብዙዎች አማልክቶች ይኖራሉ

እያንዳንዳቸው በሚያመልኳቸው ይበጃሉ/ይሰራሉ (፪x)

ብቻውን የእኔ ምሥጋና የተገባ

ሁሉ በእርሱ ከእርሱና ለእርሱ የሆነው

እግዚአብሔር ብቻ ነው

ሃሌሉያ (፰x)

ክብር ለእግዚአብሔር

እርሱ ፈጥሮ ሕያው እስትንፋስ የሰጣችሁ

የእጁ ሥራዎች በምድር ላይ ያላችሁ (፪x)

ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ በምሥጋና

የሚገባውን ክብር ያግኝና

ይክበር በምሥጋና

ሃሌሉያ (፰x)

ክብር ለእግዚአብሔር

የሰው ዘሮች በየአገራቱ ያላችሁ

ልዩ ቀለም ልዩ ልዩ ሕዝቦች በቋንቋችሁ (፪x)

ለሥሙ የሚገባውን ክብር አምጡ

በቅድስናው ሥፍራ ስገዱ

ንገሥ ንገሥ በሉ

ክብሩ ለአንተ (ክብሩ) ነው (፫x)

. (1) . አምላክ ለሆንከው

ክብሩ ለአንተ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ