Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከአንተ ሌላ አባት

Kante Liela Abat

2012 · ትራክ 3 · 6:43 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከአንተ ወዲያ አባት ላውቅ አልሻም እኔ

ከአንተ ወዲያ ወላጅ ላውቅ አልሻም እኔ (፪x)

ከአንተ ወጥቼ መጥቻለሁ

ወደ አንተም እሄዳለሁ

ጀማሬዬ አንተ ነህ

ፍጻሜዬም ደግሞ ነህ

ሌላ ላውቅ አልሻም

ከአንተ ሌላ አልሻም

ሌላ ላውቅ አልሻም

ከአንተ ሌላ አልሻም (፪x)

ላርቅህ አልፈልግም ላርቅህ ውዴ

ላርቅህ አልፈልግም ላርቅህ እኔ ሆይ

ላርቅህ አልፈልግም እጠጋሀለሁኝ አብዝቼ

የወለድከኝ ነህ ወላጄ አባብዬ (፪x)

ሰማይ ምድርን የፈጠረ

ታላቅ አምላክ የሆነ

ከሁሉ በላይ ከፍ ያለ (ከፍ ያለ)

የሁሉ የበላይ የሆነ

እግዚአብሔር መንፈስ

ለእኔም ደግሞ አባት (፪x)

ከአንተ ወዲያ አባት ላውቅ አልሻም እኔ

ከአንተ ወዲያ ወላጅ ላውቅ አልሻም እኔ (፪x)

ከአንተ ወጥቼ መጥቻለሁ

ወደ አንተም እሄዳለሁ

ጀማሬዬ አንተ ነህ

ፍጻሜዬም ደግሞ ነህ

ሌላ ላውቅ አልሻም

ከአንተ ሌላ አልሻም

ሌላ ላውቅ አልሻም

ከአንተ ሌላ አልሻም (፪x)

ከአለም ፍጥረት አስቀድሞ

ያወቀኝ ከእናት ቀድሞ

ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም (ሌላ አላውቅም)

ወላጄ የምለው ሌላ የለኝም

እግዚአብሔር መንፈስ

ለእኔም ደግሞ አባት (፪x)

ላርቅህ አልፈልግም ላርቅህ ውዴ

ላርቅህ አልፈልግም ላርቅህ እኔ ሆይ

ላርቅህ አልፈልግም እጠጋሀለሁኝ አብዝቼ

የወለድከኝ ነህ ወላጄ አባብዬ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ