ከጠዋት አንስቶ
Ketewat Anseto
2012 · ትራክ 7 · 7:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቅም ስጠኝና አብዝቼ ልውደድህ
መቼም ልጥገብህ አልል አንተ አትጠገብም
ሰው ቢያንገራግር እስከሚገባው ነው
የበራለት ለታ ለመውጣት የሚያስቸግር
ፍቅርህ እጅግ ብርቱ ነው
አዝማች · Chorus
ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ
ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ
ብትወደድ አትጠገብም (፫x) የእኔ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ ኢየሱስ
ላልወድህ አልችልም ላልቀርብህ አብዝቼ
የተገኘሁብህ አንተ እኮ ነህ ምንጬ
እጅግ ጥልቅ ነው ያለን ትስስር
ከጥንት የነበረ ዛሬም ያለ ለዘለአለም
የሚቀጥል ነገር
አዝማች · Chorus
ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ
ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ
ብትወደድ አትጠገብም (፫x) የእኔ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ
ቁጥር 3 · Verse 3
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ ኢየሱሴ
ከጥንት ከማለዳ የኔ ያንተ ነገር
ማቆምያም የለውም ጊዜያትን ሲሻገር
ሁሉ ነገር ያልፋል አንድ ሳይቀር ጠፊ ነው
ለኔ ያለህ ነገር እኔም ላንተ ያለኝ ነገር
ዘለዓለም ኗሪ ነው
አዝማች · Chorus
ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ
ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ
ብትወደድ አትጠገብም (፫x) የእኔ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ
ቁጥር 4 · Verse 4
እወድሀለሁ (፫x) ጌታ ኢየሱስ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ