Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ ዘለዓለም ነህ

Ante Zelalem Neh

2012 · ትራክ 5 · 4:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ

ውሆችን በእፍኝህ የሰፈርህ

ሰማየ ሰማያት የአንተ ናቸው

በግርማዊነትህ ሰራሃቸው

ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ

ለዘለአለም የምትኖር (፪x)

አንተ ዘለአለም ነህ (፪x)

ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ

ጌታ አልፋና ኦሜጋ (፪x)

ሰማይና ምድር በስፍራቸው

ሳይኖሩ አንተ ነህ ቀድመሃቸው

ጅማሬ የለህም ፍጻሜ

እድሜህ አይሰላ ሰው አይደለህ

ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ

ለዘለአለም የምትኖር (፪x)

አንተ ዘለአለም ነህ (፪x)

ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ

ጌታ አልፋና ኦሜጋ (፪x)

ከአማልክት መሃከል እንደአንተ ማን ነው

የእኔን ጌታ እግዚኣብሔር የሚመስለው

አምላኬ ከሁሉም ትለያለህ

አንተ የአማልክት ሁሉ አምላክ ነህ

ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ

ለዘለአለም የምትኖር (፪x)

አንተ ዘለአለም ነህ (፪x)

ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ

ጌታ አልፋና ኦሜጋ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ