Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የመውደዴ ብዛት

Yemewdedie Bzat

2012 · 5:53 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የመውደዴን ብዛት የፍቅሬንም ብዛት

በውስጤ ያለውን የንዳዱን ብርታት

የማረከኝን የተረታሁልህን

ልገልጠው አልችልም አንተ ያረክልኝን (፪x)

አሸንፈኸኛል እመሰክራለሁ

ጌታ አፌን ሞልቼ እናገራለሁ (፪x)

የአንተ ፍቅር ውስጤ ያለው

እየጨመረ የሚሄድ ወንዝ ነው

አሁንስ አየሁ ይህ ገብቶኛል

የማልወጣው ነገር ይዞኛል (፫x)

የምልህ አለኝ የምልህ

ቋንቋን አጥቼ ያኖርኩልህ

ቃላት አግኝቼ መጥቻለሁ

ኢየሱስዬ ወድሃለሁ (፪x)

ኧረ ማን ሊተካህ አንተን (፪x)

ስፍራህን የሚወስድ ከወዴት ሊገኝ

በሰማይ የለም በምድርም የለም

ከምድርም በታች አይገኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ