ማነው ማነው
Manew Manew
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው
ማነው ማነው በስራ ላይ የሚያውለው
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝናብ ቢመጣ ጐርፍ ቢመጣ ነፋሱ ቢነፍስ
በአሸዋ የሰራ በአለት የሰራ ስራውን ይፈትሽ
ቁጥር 2 · Verse 2
ማነው ማነው በአለት የሰራ ልባሙ ሰው
ማነው ማነው ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው
ዝናብ ቢመጣ ጐርፍ ቢመጣ ነፋሱ ቢነፍስ
ጸንቶ ቀረ አልወደቀም ፈተናውም ቢብስ
ቁጥር 3 · Verse 3
ማነው ማነው በአሸዋ የሰራ ሰነፉ ሰው
ማነው ማነው ቃሌን ሰምቶ እምቢ ያለው
ዝናብ ቢመጣ ጐርፍ ቢመጣ ነፋሱ ቢነፍስ
ቤቱን መታው አፈራረሰው ባዶ አደረገው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው
ማነው ማነው በስራ ላይ የሚያውለው
ቁጥር 4 · Verse 4
ቃሉን ሰምቼ ጌታን አምኜ ድኛለሁና
ብልህ ነኝ እኔ ቤቴን በአለት ላይ ሰርቻለሁና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ