ምንም ታሪክ የለኝ
Menem Tarik Yelegn
2007 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔም እንደሌላው አለሁኝ ነበርኩኝ ብዬ ምናገረው
ከበደሌ ሌላ ምንም ነገር የለኝ የምዘረዝረው
ሰው መስሎት ቢክበኝ ሁሉን እንደከንቱ ቆጥሬ እተዋለሁ
ይልቁን በሞቱ ጌታን እንድመስለው ለዚያ እዘረጋለሁ
አዝማች · Chorus
እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ
ከመቃብር ወዲህ ቀሪ የሆነውን ታሪክ ከምሰራ
ጊዜ የሚሽረውን ነገ የሚረሳውን ዝና ከማወራ
ዘላለማዊውን ሕይወት የሆነውን ላውዛ ያንን ዜና
የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የጌታችን ታሪክ እርሱ ይበልጣልና
አዝማች · Chorus
እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ
ከአምላክ ጥሪ ሰምተው ለአምላካቸው ወንጌል ሌት ቀን የሚለፉ
በዚያ በማይጠፋው በሕይወት መጽሃፍ ላይ ተግተው የሚጽፉ
በበጉ ዙፋን ፊት በጻድቃን ማህበር ስማቸው ሲጠራ
በነፍስ ተወራርደው ድል እንዳደረጉ በአንክሮ ሲወራ
አዝማች · Chorus
እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ
ጥላዋ እስክታልፍ ጀንበር እስክትጠልቅ በአምላኬ ታግዤ
በሚሰጠኝ ጸጋ የጸድቅን ጐዳና እስከጫፍ ተጉዤ
ቃል እንደገባልኝ ለእረፍት ሲጠራኝ አክሊል ቢጠብቀኝ
ከሁሉም የሚበልጥ የነፍሴ መድኃኒት ፊት ነው የሚናፍቀኝ
አዝማች · Chorus
እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
እኔን ብትጠይቁኝ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ
ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ