ማን እንደ እግዚአብሔር
Man Ende Egziabhier
2007 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘንዶውን የወጋህ እባቡን የረገጥክ
ባህሩን ሰንጥቀህ ህዝብህን ያሻገርክ
በክብር ያረገህ በክብር የምትመጣ
አንተ አይደለህም ወይ ነፃ የምታወጣ
አንተ አይደለህም ወይ
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንደ እግዚአብሄር ያለ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ተዋጊ
የገሃነምን ዘር ገርስሷል
ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የእነ ሲድራቅ አምላክ የዳንኤል ታዳጊ
ከእቶን የምታድን የአምበሳን አፍ ዘጊ
በዘመናት ሁል ከህዝብህ ጋር የቆምክ
በከሳሻቸው ፊት ልጆችህን ያስከበርክ
አንተ አይደለህም ወይ
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንደ እግዚአብሄር ያለ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ተዋጊ
የገሃነምን ዘር ገርስሷል
ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃያላን በግርማ ፈጥነው ሲሟሽሹ
በአክብሮት በፍርሃት ከፊቱ ሲሸሹ
መራፉን ይዘጋል ፍጥረት በቀጠሮ
ጌታ ብቻ ይኖራል ዘላለም ተከብሮ(፪)
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንደ እግዚአብሄር ያለ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ተዋጊ
የገሃነምን ዘር ገርስሷል
ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ይሄ ታላቅ አምላክ እኛን ከመረጠን
በጸጋው ሸፍኖ ህዝቤን አጅብ ካለኝ
አንተ ብቻ አምላክ ሁንልን ብለናል
ታቦቶቻችንም በእግርህ ስር ጥለናል
ለአንተ ተማርከናል
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንደ እግዚአብሄር ያለ ታዳጊዬ
ለሚታመኑበት ተዋጊ
የገሃነምን ዘር ገርስሷል
ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ጠላቴ አፍሮ ተመልሷል
ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል(፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ