አንዴ ቆርጠናል
Andie Qortenal
2007 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰልፉ ተከማቸ ጦር ተወረወረ
የወንጌሉን ዘማች ያዙልኝ ተባለ
የሞት ጥላ ረዝሞ ለሰሚው ቢያስፈራም
መጋደልን ለምደናል ለአምላካችን ስራ
አዝማች · Chorus
አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል
በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስጋው ለመከራ ቁርበቱን ለአለንጋ
አማኝ የሚያቀርበው ላመነበት ዋጋ
እንደዚህ ከሆነ አምላክ ይሁን ያለው
እንኳንስ መከራ ይሁን የፈቀደው
አዝማች · Chorus
አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል
በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የመድህኑን ተስፋ ባይገነዘቡ
ስለ ሽልማቱ መዋረድ ኮከቡ
አምላክ ባይኖርለት ተረስቶ ነበር
ትላንት የታደገው ዛሬም በእርግጥ አለ
አዝማች · Chorus
አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል
በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በስጋችን ፈርደን በነፍስ ቆርጠናል
የደህንነት ጉዞ አንዴ ጀምረናል
ወድቀንም ተነስተን ይህን ሁሉ ስናልፍ
በድል እንዘጋለን የሕይወትን ምዕራፍ
አዝማች · Chorus
አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል
በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ