የእኔ መድህን ጌታ
Yenie Medhen Gieta
2007 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬን ልባርክ አፌን እከፍታለሁ
ለወደደኝ ጌታ ምስጋናን እሰዋለሁ ተመስገን እላለሁ
በመከራ ጊዜ ፈጥኖ ደርሶልኛል
ነፍሴ ትገዛለት ፍቅሩ አሸንፎኛል (፪x)
ለመድህኔ ይሁን ምስጋና
ድሃ አደጉን አስቧልና
የሚያረካ ፈጸሞ በአለም
እንደ ኢየሱስ የለም
አዝማች · Chorus
ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው
ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ
ስሙ ምን ጊዜም የሚረታ
ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ
የእኔ መድህን ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
ብርቱ መታጠቂያው ድንገት ሲላላበት
የጦረኛው መውጊያው ጦር ሲሰበርበት (፪x)
ተከላካይ ጋሻው ከእጁ ሲወድቅበት
መከታ ነው ያለው ተገኔ ነው ያለው ምሽግ ሲናድበት
መድህኔ ግን ሁሌ ባለ ድል
ድል አድራጊ ክንዱ የማይዝል
ታላቅ አምላክ የኔ መከታ
ሁሌ የሚረታ
አዝማች · Chorus
ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው
ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ
ስሙ ምንጊዜም የሚረታ
ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ
የእኔ መድህን ጌታ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሆ እየተባለ ተስፋ የተጣለበት
በጊዜው የሰው ልጅ የተጋደለበት የተራረደበት
ዛሬ ተረት ሆኖ በትዝብት ይወራል
የኢየሱስ ነገር ግን እያደር ያብባል እያደር ይጥማል
የእግዚአብሄር ልጅ ሁሌ አሸናፊ
የጠላቱን ድፍረት ገፋፊ
በዙፋን ላይ ሁሌ የሚኖረው
ኢየሱስ ጌታ ነው
አዝማች · Chorus
ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው
ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ
ስሙ ምንጊዜም የሚረታ
ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ
የእኔ መድህን ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ