ጌታዬን አከብራለሁ
Gietayien Akebralehu
2007 · ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አነባ ጌታዬ አፈር ላይ ተደፍቶ
የወደቀበትን ጭንቀት ተመልክቶ
ጌታዬ ተጨንቆ አባዬ ሆይ አለ
አጋዥ አልተገኘም ለጌታ የዋለ
መስቀል ተሸክሞ ትከሻው ተላጠ
ግርፋቱ በዛ ገላዉ ተመለጠ
ራቁቱን ደም ሲያፈስ በቀራንዮ ዋለ
አንገቱ ደፋ ሲል ዕዳ ተከፈለ
አዝማች · Chorus
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዝናን ከበሬታን ሞገስን በሥጋ
ሊያገኝ ወዶ ነፍሱን ከዓለም ከሚያስጠጋ
ይሻላል ጭጋፉ ውዳቄን እኔን መሳይ
በሥጋው ተንቆ በእምነት ጌታን የሚያይ
አዝማች · Chorus
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ማቆ በመከራ ጐስቋላ አካል ይዞ
በረሃን የሚዘልቅ ጌታን ተመርኩዞ
ተሸማቆ ኑሮውን ለጌታ ሲል ችሎ
ያለፈን አየሁት አክሊል ተቀብሎ
አዝማች · Chorus
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
በሞቱ ሊመስለዉ ጌታን ተከትሎ
ወድቆም የሚነሳ አልሸነፍ ብሎ
ለጠላቱ ታግሎ የማታ የማታ
ጌታው ምሎለታል እርሱ እንደሚረታ
አዝማች · Chorus
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ጌታዬን አከብራለሁ (፫x) በኑሮዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ