በአለንጋ አልገታኝም
Bealenga Algetagnem
2007 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በአለንጋ አልገታኝም የበረት ዘንግ ይዞ
አላስማረከኝም ሰይፉን በኔ መዝዞ (፪x)
ከዚህ በሚበልጥ ኃይል በፍቅሩ ጎበኘኝ
ጉልበቴን አስገዛ መስቀሉን ሊያሳየኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን
ቃልህም አጸናው መሠረቴን
ቁጥር 2 · Verse 2
መከራ ስቧጥጥ ጉዞ ሲከብድብኝ
ተንሸራትቼ እንድወድቅ ከስር ሲናድብኝ (፪x)
የድል ቀን ቢነጋ ኢየሱስ ሞተና
በጠላት ተጫማሁ ኃይል አገኘሁና (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን
ቃልህም አጸናው መሠረቴን
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጐንህ ፈስሶልኝ ፍቅርህን ጠጥቻለሁ
ከተበሳው እጅህ ሆዴን ሞልቻለሁ (፪x)
የእግሮችህ ቀዳዶች ያጫሙኝ ጠላት ላይ
የራስህ ላይ እሾህ ሆነኝ ክብርህን እንዳይ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን
ቃልህም አጸናው መሠረቴን
ቁጥር 4 · Verse 4
ኑሮዬ ይገባሃል አንተ ሚስጥረኛዬ
የነፍሴ ፍላጎት ይሄ ነው ጌታዬ (፪x)
ጠላት አደናግጦ ልክድህ ሲያባብለኝ
ያንተን ጣራ አስቤ እንድመለስ እርዳኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x)
መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን
ቃልህም አጸናው መሠረቴን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ