አባቴ ኢየሱስ
Abatie Eyesus
2005 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ
አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት
ከጭንቀት ማሳረፍ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የደረሰበት ያውቃል ተስፋው የጨለመበት
በቃ አለቀ ብሎ ሞቱን ሲጠባበቅ
ድል በድል አድራጊው ጌታዬ ደርሶለት
ሳቅ በሳቅ ያረገው ከላዩ ገፎለት (፬x)
አዝማች · Chorus
አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ
አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት
ከጭንቀት ማሳረፍ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምድረ በዳ ውስጥ አጋር እንዲያ ተጨንቃ
ሲሞት እንዳታየው ልጇን አርቃ ጥላ
ድምጿን አሰምታ በጣም አለቀሰች
ማነው ሚደርስልኝ ኧረ ማነው አለች
እግዚአብሔር ከሰማይ ድምጻቸውን ሰማ
የጨለመውን ሕይወት እንደገና አበራ (፬x)
አዝማች · Chorus
አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ
አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት
ከጭንቀት ማሳረፍ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሞት ፍርሃት መጥቶ ዙሪያዬንም ከቦኝ
መሄጃ ማምለጫ ሁሉም ግራ ገብቶኝ
ተጨንቄ ሳለሁ ጌታ ደርሶልኛል
ሸክሜን አራግፎልኝ በደስታ ሞልቶኛል (፬x)
እንደሰው አይደለም (፰x)
ይገርመኛል እዚህ መድረሴ (፪x)
ይገርመኛል ሰው መሆኔ
ይገርመኛል እኔ ማለፌ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ